ቆብ ኣርጎ ጠለፈኝ
ሲወራ ሰምቼ በዝና፤
ጥርብ ያለ ቁመና..ወ-
እጅጉን ነው ኣሉት መልከቀና፤
ሲሰማራ የሰው ልብ ኣደና
ሞት ኣይፈራ ጀግና፤
ጎባጣ ሥርኣት የሚያቃና::
ታድያ በወሬ ግፊት:
ጉደኛቱ! ወድጄው ሙትት፤
ብር ብዬም ወዳለበት ጥፍት::
ሳልውል ሳላድር፤
መልኩም ሳላወዳድር፤
ልቤም ሳላመካክር፤
ነገርተኞች ለፍትሕ ሲያደራድር፤
ደፍሮም ሲዋጋ ለክብር፤
ሳላይ እንዳልመሰክር፤
የወሬ ዱሪቶን ድርብርብ:
ጨለማም ክንብብንብ:
-------- ኣድርጎ ----
ገደል ጫፍ ላይ ቆሞ ሲዘምር:
ክንፍዋ እንደተሰበረ እርግብ፣
ቆብ ኣርጎ ጠለፈኝ:
መርበብ ውሰጥ እንደምርኮኘቹ ሊከተኝ፤፤
ዋ! ሰው ሁሉ ሲያወራ፣
ምን ነው ቢያክለበት ትንሽ የሓቅ ጮራ፤፤
ኃይለሥላሴ ግርማይ
9/9/2003